Made by Devi AI By using this website, you agree to the following terms and conditions

GRADE 9
BIOLOGY

PYTHON TUTORIAL

ሰላም ውድ ተማሪዎች ይህ PYTHON TUTORIAL ነው ፒስ ናችሁ ኣ🫡 እኛ አለንላችሁ እንግዲህ ዛሬ Biology Chapter One ን በይፋ እንጀምራለን ወንድም 👱🏼‍♂️እና እህቶቼ 👩🏼‍🦳 ፏቧ እያላችሁ በመሃል ውሃ ነገር 🫗እየተጎነጫችሁ አብራችሁን ቆዩ 🥱አይፈቀድም እናንተ ሃሳባችሁን ስጡን እኛ Concept ኡን እናስጭብጣቹሃለን let us get down🙃  
 
   👉 INTRODUCTION TO BIOLOGY

 ☑️ 1.1 Definition of Biology


# The word Biology come from two Greece words 'bios' means life and 'logos' means study. so, the term biology can be defined as the study of life.
      ባዮሎጂ የሚለው ቃል ከሁለት የ ግሪክ ቃላት የመጣ ነው እነዚም ቃላት ባዮስ ትርጉሙ ህይወት እና ሎጎስ ትርጉሙ ጥናት የሚሉ ናቸው ስለዚህ ባዮሎጂን define ስናደርገው ስለ ህይወት የሚደረግ ጥናት ነው ማለት እንችላለን (ያው ይሄን ታች ክፍል ላይ በደምብ ተምራችሁታል)

✔️Biology is the scientific study of life or living things.

        መፅሃፋችሁ Biology ን define ሲያደርገው ህይወት ስላለው ነገር ወይም ስለራሱ ስለ ህይወት የሚደረግ ሳይንሳዊ ጥናት/ምርምር ነው ብሎ ያስቀምጣል። ለመሆኑ ህይወት ያለው ነገር / ህይወት ስንል ምን ማለታችን ነው? ሳይንሳዊ ጥናት ማለትስ? ሁለቱንም ተራ በተራ ቀጥለን እንመልከት....

❓ What does it mean to be “alive”? 

▪️ It seems very difficult to objectively define life in a simple sentence. But, we recognize life mainly by common characteristics shared by living systems. 
 Life (ህይወትን) በ አንድ ቃል፣ ሃረግ ወይም በ አንድ ዓ.ነገር መግለጽ እጅግ አስቸጋሪ ነው። ቢሆንም ግን ህይወት ያላቸው ነገሮች ከሚያሳዩት ተመሳሳይ ባህርይ(መገለ) በመነሳት የህይወትን ምንነት ልንገነዘበው እንችላለን። ለመሆኑ ህይወት ያላቸው ነገሮች ሁሉ ሊያሳዩአቸው የሚችሏቸው ባህርያት ምን ምንድናቸው? ቀጥለን እንመልከት......
     
 ✍🏻 Living things: ህይወት ያላቸው ነገሮች፥

   • are composed of one or more cells 
        ከ አንድ ወይም ከ አንድ በላይ ከሆኑ ህዋሳት(cells) የተገነቡ ናቸው
   • can respond to stimuli, grow, reproduce, etc. 
       በአካባቢው ላለ ማንኛውም አይነት ለውጥ ምላሽ ይሰጣሉ, ያድጋሉ(በ አካል) እንዲሁም ይዋለዳሉ
   • transmit genetic information to their offspring
        Genetic info(DNA, RNA) ያቸው ወደየ ዝርያዎቻቸው ይተላለፋል🪿🐣
   • need the energy to accomplish work
       ለማንኛውም ውስጣቸው ለሚከናወን chemical process ወይም በውጭ ለሚያደርጉት ተግባር ጉልበት(Energy) ወይም በአጭሩ ምግብ ያስፈልጋቸዋል
   • can maintain relatively constant internal conditions (homeostasis)
      ውስጣዊ ስርዓታቸው ቋሚ ነው 🤔 ለማስረዳት ይከብዳል ብቻ እንዲገባችሁ አንድ ምሳሌ ልጠቀም የሰው ልጅ አማካይ የሰውነት ሙቀት መጠኑ 37°c ነው ከዚ በጣም ከፍ ሊል አይችልም ደግሞ ዝቅ ሊልም አይችልም እልም ያለ በርሃም ሂዱ በጣም ቀዝቃዛ ቦታም ሂዱ አማካይ የ ሙቀት መጠናችሁ የሚቀየር አይደለም
   • are capable of evolutionary adaptation to the environment 
       የ አካባቢ ለውጦችን ( እንደ የ አየር ንብረት ለውጦችን) ተላምደውመኖር ይችላሉ  
   > are complex and highly ordered
        ይሄን ሃሣብ ለማስረዳት የሰው ልጅን እንደ ምሣሌ እንውሰድ 🙎 ሰው ከ living things አንዱ ነው ታድያ ሰው ሰው የሆነበትን የሰውነት መዋቅር ስንመለከት በመጀመርያ ህዋስ(cell) ይኖራል ይህ cell ከሌሎች ሴሎች ጋር አንድ ላይ በመሆን ህብረህዋስ(tissues) ይሰራል እነዚህ ህብረ ህዋሣት ደግሞ አንድ ላይ በመሆን የሆነ አካል(organ) ይሰራሉ ለምሣሌ ልብ ኦርጋን ነው ሣንባም ኦርጋን ነው ልብን ለመገንባት የሚውሉ ህብረህዋሣት የልብ tissues ይባላሉ እነዚህን የልብ tissues ለመገንባት የሚውሉ ሴሎች አሉ እንደገና ደግሞ የሣንባ tissue ለመስራት የሚውሉ ሴሎችም አሉ እንደ ልብ እና ሣንባ ያሉ አካላት ደግሞ አንድ ላይ በመሆን የአካል ስርዓት(organ system) ይሰራሉ እነዚህ organ systems ደግሞ አንድ ላይ በመሆን ሰው የሚባል organism ይሰራሉ እደምታስቡት ቀላል አይደለም በጣም ውስብስብ መዋቅር ነው ለዛም ነው living organisms are complex and highly ordered ያልነው
       cell + cell = tissue + tissue = organ + organ = organ system + organ system = organism
 ☝ ይሄን እንዳትረሱት
    

  ❓ What is a scientific study? 

Biologists study about living things using a scientific method that involves asking questions, suggesting possible answers; and testing for the validity of the answers through experimentation. 

Biologist ች ህይወት ስላለው ነገር ጥናት ሲያደርጉ ሳይንሳዊ ዘዴን ይጠቀማሉ ይህ ዘዴ በውስጡ ጥያቄ የመጠየቅ ( observation)፣ ለጥያቄዎቹ እውነት ሊሆኑ የሚችሉ መልሶችን የማግኘት እና የተገኙትን መልሶች እውነተኛነት በ experiment የማረጋገጥ ሂደቶችን ያቀፈ ነው። 

  ☝🏻ለምሳሌ፥ እናንተ ዒዩግሊና (Euglena) ከቦታ ቦታ ቦታ በምኑ እደሚንቀሳቀስ ጥያቄ ፈጠረባችሁ እና ጓደኛችሁን ጠየቃችሁት እሱም ፍላጄለም (Flagellum) የሚባል መንቀሳቀሻ አካል እንዳላቸው ያነበብኩ ይመስለኛል ብሎ መለሰላችሁ ከዛ Laboratory ገብታችሁ ማይክሮስኮፕ 🔬በመጠቀም በእርግጥም ዒዩግሊና ፍላጄለም እንዳለው አረጋገጣችሁ። በቃ ሳይንሳዊ ዘዴ (scientific method) ማለት ይሄው ነው ጥያቄ ማንሳት፣ ለጥያቄው መልስ መፈለግ ከዛ መልሱን በስራ ማረጋገጥ አለቀ 😎


♦️What relationships does Biology have with other fields of natural sciences? 

   በ 1.1 ስር ያለውን የመጨረሻ ሃሳብ እናንሳ Biology ከሌሎች የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፎች ጋር ያለው ግንኙነት ምንድነው? 

  The study of biology is a point of merging information and tools from all natural sciences. 
    biology ጥናት ሲያካሄድ ከ ሌላ የ ሳይንስ ዘርፍ መረጃዎችን፣ የጥናት ውጤቶችን ወይም ለጥናቱ የሚረዱ መገልገያ መሳርሳዎችን ሊጠቀም ይችላል።

 For example scientific concept like conversion of radiant energy into organic molecules by photo-synthesis is studied with the knowledge of chemistry and Physics. 
  ለምሳሌ፥ እጽዋት ከ ፀሐይ energy እንዴት ምግባቸውን እንደሚያዘጋጁ ወይም ስለ photo-synthesis process ጥናት እንዲደረግ ቢፈለግ የ physics, chemistry እና biology እውቀት የግድ አስፈላጊ ይሆናል።


እሺ ውድ ተማሪዎች 1.1 ይሄን ይመስላል
ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ጥያቄ ካለ @Python305
በተረፈ ሁሉም ነገር ከ 👨🏾‍🎓🧑🏻‍🎓 በኋላ ይደርሳል
so, more ትኩረት ለ 📚 እወዳችኋለሁ መልካም ግዜ🫡

ሰላም የተወደዳችሁ 🙋🏻‍♂️ እንዴት ናችሁ ይህ PYTHON TUTORIAL CLASS ነው! class እንዴት እየሄደ ነው? አሪፍ እንደሚሆን አልጠራጠርም😊 እንግዲህ ዛሬ የምናየው 1.2 ''Why do we study biology'' የሚለውን ይሆናል እንደተለመደው ፏቧ በሉ💃🏼🕺🏻 ውሃ ምናምን ደግሞ ጠጡ እሺ ግብዣው በኔ ነው 😜 በሉ ወደ ክላሳችን እንግባ......


☑️1.2 Why do we study Biology?


▪️ ለምንድነው Biology የምናጠናው(የምንማረው)? በጣም ወሳኝ ጥያቄ ነው ምክንያቱም ለምን እንደምንማር የማናውቅ ከሆነ ትምህርቱ ሊገባን በሚገባው ያህል አይገባንም ወይም አንረዳውም ካልተረዳነው ደግሞ ልንጠቀምበት አንችልም የማይጠቅመን ከሆነ ደሞ መማራችን ከንቱ ልፋት ነው ጊዜ ማባከን ብቻ ይሆንብናል ስለዚህ መማራችን ኪሳራ እንዳይሆንብን የምንማርበትን ምክንያት ቀጥለን እንመልከት.....


 ✔️ Studying biology helps to understand how living things work, how they function and interact with the environment. 
  ▫️ባዮሎጂ የምንማርበት ዋና አላማ ህይወት ያላቸው ነገሮች በአካባቢያቸው ላለ ነገር (environment) በዋናነት ለሰው ልጅ ምን አይነት ጥቅም አላቸው ወይም ከ አካባቢያቸው ጋር ምን አይነት ግንኙነት አላቸው የሚለውን ሃሳብ ለመረዳት ነው።


 ✔️ Biology touches our everyday life in many ways. For example, biologists have discovered drugs that are used to treat different human diseases. 
   ▫️ባዮሎጂ በብዙ አቅጣጫ የዕለት ተዕለት ኑሯችንን ይዳስሳል ( በአብዛኛውን የ ዕለት ተዕለት ተግባሮቻችንን የምናከናውነው የባዮሎጂን እውቀት በመጠቀም ነው።
   ለምሳሌ ባዮሎጂ የሰው ልጅን ሊያጠቁ ለሚችሉ በሽታዎች መዳኒት በማዘጋጀት ላይ ትልቅ ሚና አለው። እስቲ ባዮሎጂ በየዕለት ኑሯችን ላይ ያለውን ድርሻ በተወሰነ መልኩለማየት እንሞክር........


    🔘 Application of Biology in our day to day life: 


📌Wine-making, the brewing, the baking of bread and the production of cheese all depend on fermentation processes brought about by yeasts, other fungi and bacteria, or enzymes from these organisms. 
    ▫️እንደ ወይን እና ቢራ ያሉ የ አልኮል መጠጦች🍷 የሚዘጋጁት በ እርሾ ባክቴሪያዎች እና ፈንገሶች እንዲሁም ኤንዛይሞች አማካኝነት ነው ያው እናንተ እንኳን መጠጥ አትጠጡም😜 ስለዚ ባዮሎጂ ለናንተ ዳቦ 🍞 እና አይብ (cheese) 🍚 አዘጋጅቶላቹሃል😂። እንደ ዳቦ እንጀራ እና አይብ የመሳሰሉ ምግቦችን ለማዘጋጀት የባዮሎጂን እውቀት እንጠቀማለን። ቆይ ቆይ ግን እናቶቻችን የባዮሎጂ እውቀት አላቸው ማለት ነው?🤔 አዎ እናቶቻችን በልምድ ያገኙት የ ባዮሎጂ እውቀት አላቸው እኛ ዛሬ ላይ እየተማርን ያለነው ጥንት የነበረውን የ እናት አባቶቻችንን እውቀት ባዮሎጂስቶች ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እና ይበልጥ ዘመናዊ በሆነ መንገድ አስቀምጠውል ነው እንጂ ትናንት እና ከትናንት ወድያ በመጣ ፍልስፍና አይደለም።
         
  📌 Antibiotics, such as penicillin, are produced by mould fungi or bacteria. 
      ▫️እንደ ፔኒሲሊን ያሉ ፀረ-ባክቴሪያ ክትባቶች እና መድሃኒቶች የሚዘጋጁት ከ ፈንገስ እና ባክቴሪያዎች ነው። ስለ ፔንሲሊን ሌላ ግዜ በደንብ እንማራለን።


 📌 The production of industrial chemicals such as citric acid or lactic acid needs bacteria or fungi to bring about essential chemical changes. 
      ▫️ብዙ ግዜ አስፈላጊ ለሆኑ የ ኬሚካል ፕሮሰሶች እንደ ሲትሪክ አሲድ እና ላክቲክ አሲድ በ ኢንዱስትሪ ወይም በላቦራቶሪ ውስጥ ይዘጋጃሉ እነሱን ለማዘጋጀት ደግሞ ባክቴሪያ ወይም ፈንገስ ወሳኝ ነገር ነው።


📌 Sewage disposal depends on bacteria in the filter beds to form the basis of the food chain that purifies the effluent. 
      ▫️ይሄን እንዴት ልበላችሁ መሰላችሁ ለምሳሌ በአይን ሊታዩ በማይችሉ ዘ-ኣካላት የተበከለን ለሰውነታችን መርዛማ የሆነን ውሃ በ ባክቴሪያ ማከም እና ለመጠጥ እንዲሆን ማድረግ ይቻላል። ለጊዜው ሃሳቡን ማወቃችሁ ይበቃል ሂደቱን ሌላ ግዜ እናያለን አሁን ላይ አይጠቅማችሁም።


📌 Discovery of the structure of DNA and forensic analysis of DNA samples from crime scenes.
     ▫️አሁን ላይ ብዙ ግዜ በተለይም በ ፍርድ-ቤት ኬዝ የልጅነት እና ወላጅነት ማረጋገጫዎች(DNA) አስፈለጊ ሆነው ይገኛሉ ከ DNA ጋር የተያያዘን ጉዳይ ደግሞ ያለ ባዮሎጂ እውቀት አይታሰብም❌


👉 ስለዚህ እኚህ ከላይ የጠቀስናቸው ጉዳዮች ሁሉ ተፈፃሚነት የሚያገኙት በ ባዮሎጂ እውቀት ነው። So, ባዮሎጂ በህይወት እንቅስቃሴያችን ውስጥ ያለው ድርሻ ምን ያህል እንደሆነ የተረዳችሁ ይመስለኛል 👍
 
  
እሺ የተወደዳችሁ ተማሪዎች 1.2 ይሄን ይመስላል
ሃሳብ፣ አስተያየት ጥያቄ ካለ ይኸው @Python305
በተረፈ እንደ ሁልግዜው የምላችሁ ሁሉም ከ 👨🏾‍🎓🧑🏻‍🎓
በኋላ ይደርሳል so, more ትኩረት ለ 📚 እወዳችኋለሁ
መልካም ግዜ 🫡

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon......

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon......

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon......

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon.....

Coming soon...